follow_us:
📞 +251 911 898 192

የሀላባ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ለሀላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ አባላት የ5 ሚሊየን ኮደርስ ስልጠና ሰጠ ።

📅 August 11, 2025 | 🖊️ Admin

News Image

ነሀሴ 2/2017 ዓ.ም

 የሀላባ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ የ5 ሚሊየን ኢትዮኮደርስ ስልጠና የመስጠት ስራ አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በዛሬው እለትም ለሀላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ አባላት የ5 ሚሊየን ኮደርስ ስልጠና ሰጠ ። በስልጠናው ወቅት የዞኑ ሳይንስና ቴክኖሎጂ መምሪያ የሶፍትዌር ልማት ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ አቶ አለሙ አሰሞ በስልጠና መረሀግብሩ ላይ አጠቃላይ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ሂደት ምንነት ላይ ሙያዊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ‎ የኮዲንግ ስልጠናው በትኩረት እየተሰጠ ከሚገኝባቸው ዞኖች አንዱ የሀላባ ዞን ሲሆን ይህም ስልጠና በቀጣይነትም ለሌሎች ተቋማት ባለሙያዎችም የመስጠት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል ። በአሁን ወቅት በርካታ የዞኑ ማህበረሰብ በዞኑ የኮዲንግ ስልጠና እየወሰዱ የሚገኙ ሲሆን ከነዚህም መካከል በርካታዎች ስልጠናቸውን አጠናቀው የሰርተፍኬት ባለቤት መሆን ችለዋል፡፡ ‎www.ethiocoders.et የሀላባ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ።www.ethiocoders.et

 

 

← Back to News