follow_us:
📞 +251 911 898 192

"ሴራ በዓላችን በህብር የመቻል አቅም ማሳያችን" በሚል መሪ ቃል በዞን ማጠቃላይ መጪው ጥር 3/2018 በደማቅ ይከበራል!

📅 January 9, 2026 | 🖊️ Admin

News Image
 
የዘንድሮ የሀላባ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ ሴራ በዓል በተለያዩ ታላላቅ ልማታዊ ፕሮጀክቶች ምረቃ ታጀቦ የሚከበር መሆኑ ከወትሮ ልዩ ያደርገዋል!
ግዙፉና አዲሱ የሀላባ ዞን አስተዳደር ህንጻ ግንባታ አጠቃላይ ስራው ተጠናቆ በሴራ በዓል አከባበር ዕለት ይመረቃል።
 
የሀላባ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ግንባታ የመጀመርያ ምዕራፍ ተጠናቆ ለታላቁ የሴራ በዓል መድረሱ በስፖርቱ ረገድ ብቻ ሳይሆን በባህላዊና ማህበራዊ ትስስር ላይም ትልቅ አዎንታዊ ተፅዕኖ ያስገኛል።
የዘንድሮው የሴራ በዓል በዚህ አዲስ ኢንተርናሽናል ስታዲየም መከበሩ ለበዓሉ ልዩ ድምቀት ከመስጠቱም በላይ የህዝቡን የልማት ተሳታፊነትና የአንድነት አቅም ያሳያል።
"ሴራ በዓላችን በህብር የመቻል አቅም ማሳያችን" የሚለው መሪ ቃል በዓሉ ከባህል ባለፈ የሰላም፣ የፍትህና የአብሮነት ተምሳሌት መሆኑን በግልጽ ያሳያል። ስታዲየሙ መመረቁ ደግሞ ይሄንን እሴት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግረዋል።
እነኚና ሌሎች በመንግስትና በግሉ ዘርፍ የተሰሩ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው በዕለቱ የሚመረቁ ሲሆን ለሀላባ ህዝብ እና ወጣቶችና ለስፖርት ቤተሰቡ ትልቅ እድል ከመፍጠሩም በላይ ለከተማዋ የንግድና የቱሪዝም እንቅስቃሴ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።
በዞኑ ማዕከል ሀላባ ቁሊቶ ከተማ የሚከናወኑ የተለያዩ ፕሮጀክቶች እየተጠናቀቀ ስሆን መጪው ጥር 3/2018 በሚከበረው ሴራ በዓል በይፋ እንደሚመረቅ ተገልጿል።
← Back to News