follow_us:
📞 +251 911 898 192

በሻምበል በድሩ ሀሰን የተዘጋጀው ሀላቢሳ-አማርኛ መዝገበ-ቃላት የሞባይል መተግበሪያ የማስጀመሪያ መርሐግብር ተካሄደ

📅 January 15, 2026 | 🖊️ Admin

News Image

ጥር 5/2018 ሀላባ ቲቪ

የሞባይል መተግበሪያውን በይፋ ያስጀመሩት የሀላባ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ኤፍሬም ዘለቀ ዘመኑ የዲጂታል ዘመን በመሆኑ መፅሓፎችን በዚህ መልኩ ወደሞባይል መተግበሪያ በመቀየር ማዘጋጀት የረጅም ጊዜ የህዝቡ ፍላጎት እንደሆነ ገልፀዋል። 

በሻምበል በድሩ ሀሰን የተዘጋጀው ይህ ሀላቢሳ-አማርኛ የሞባይል መተግበሪያ በቀላሉ ለበርካታ አንባቢያን መድረስ የሚችል በመሆኑና ለአጠቃቀም ምቹ በመሆኑ ለየት እንደሚያደርገው ተናግረዋል።

በመሆኑም መሰል የሀላቢሳ የሞባይል መተግበሪያዎች በቀጣይም እንዲስፋፉ ዘርፉን መደገፍ እንደሚገባ አስረድተዋል። የመዝገበ-ቃላቱ አዘጋጅ የሆኑት ሻምበል በድሩ ሀሰን በበኩላቸው ከአምስት ዓመት በፊት "Sayichchu"/ብርሃን/ በሚል ርዕስ ያዘጋጁት ይህ መዝገበ-ቃላት ወደሞባይል መተግበሪያ እንዲቀየር በግላቸው ከፍተኛ መስዋዕትነት መክፈላቸውን ገልፀው ስራው ተጠናቆ ለዚህ በመብቃቱ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። 

አያይዘውም የሞባይል መተግበሪያው ለብዙዎች እንዲደርስና በአጠቃቀሙ ዙሪያ አንዳችን ለአንዳችን በማሳየት መረጃ መለዋወጥ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል። በሀላባ ዞን ትምህርት መምሪያ የሥርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ አቶ ጀማል አኒቻ በበኩላቸው የሀላቢሳ ትምህርት እዚህ ደረጃ እንዲደርስ በፊደል ቀረፃው ሂደት፣በመማሪያና ማስተማሪያ መፃሕፍት ዝግጅትና አርትዖት ላይ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ሲያበረክቱ መቆየታቸውን አስረድተዋል። 

በመሆኑም ሻምበል በድሩ ሀሰንን ጨምሮ በዘርፉ የሚንቀሳቀሱ ፀሐፊዎችን ማገዝና ማበረታታት የሁላችንም ሀላፊነት መሆን አለበት ሲሉ አሳስበዋል። በመርሐግብሩ ላይ የዞኑ ትምህርት መምሪያ ለሻምበል በድሩ ሀሰን የእውቅና ሠርተፊኬትና የማበረታቻ ሽልማት አበርክቶላቸዋል። 

 

የሞባይል መተግበሪያው ሊንክ

 🤳 Download App

← Back to News