follow_us:
📞 +251 911 898 192

18ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባ ዞን ተከበረ

📅 October 13, 2025 | 🖊️ Admin

News Image

ጥቅም 3/2018

በዞኑ 18ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በፓናል ውይይትና ባንድራውን በመስቀል በብሔራዊ መዝሙር ታጅቦ ተከብሯል።

18ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን "ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብስራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ" በሚል መሪ ሐሳብ በመላ ሀገሪቱ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል። በዞኑ 18ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በፓናል ውይይትና ባንድራውን በመስቀል በብሔራዊ መዝሙር ታጅቦ በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ተከብሯል።

 ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማችን ኢትዮጵያውያን የሀገር ዳር ድንበር እና ክብሩዋን ለማስጠበቅ የደም ዋጋ የተከፈለበት የነፃነት ዓርማችን ነው ተብለዋል። ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማችን የኢትዮጵያዊያን የማንነት መገለጫ እና ብሔራዊ መግባባታችን የፀናበት እንደሆነም በሰፊ ተጠቁሟል።

የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማችን የሚከበርበት ዋና ዓላማ ለሰንደቅ ዓላማ የሚገባውን ክብር በመስጠት ዜጎች የጋራ እሴቶቻቸውን የሚያጎሉበት ሀገራዊ አንድነትንና ህብረ ብሔራዊ መግባባት የሚፈጠርበት መሆኑንም ተመልክቷል። የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ የታተመ፥ የሀገራዊ አንድነትና ነፃነት መገለጫ ታላቅ የብሔራዊ ኩራት አርማ መሆኑን ተገልጿል።

የብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በሠንደቅ ዓላማ አዋጅ አዋጅ ቁጥር 863/2006 (እንደተሻሻለው) አንቀጽ 2 መሰረት በየዓመቱ ጥቅምት ወር በገባ መጀመሪያ ሳምንት ሰኞ እንደሚከበር ተደንግጓል።

በዚህ ዓመትም ሀገራዊ ወቅታዊ ሁኔታን በዋጀ መልኩ ለ18ኛ ጊዜ ከሰንደቅ ዓላማ መርሆዎች ጋር ተገናዝቦና የኢትዮጵያን ታላቅ የከፍታ ዘመን ብስራትና ማንሰራራት በሚያረጋግጡ ውይይቶች ታጅቦ በዛሬው ዕለት በመላው ሀገሪቱ ተከብሯል። የዘንድሮ ማለትም የ18ተኛ ዙር የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን አከባበርን ልዩ የሚያደረገው የዳግም አድዋ ድል ተምሳሊታችን የሆነው የህዳሴ ግድባችን የተጠናቀቅበት ማግስት መሆኑ ነው ተብለዋል።

ሰንደቅ ዓለማ የሃገራችን ኩራትና ነጻነት በመሆኑ ዜጎች የሚገባውን ክብር መስጠት እንደሚገባ በሰፊው ተመልክቷል። ሰንደቅ ዓለማ የሕብረብሔራዊ መግለጫና የሃገር ፍቅር ነው ያሉት የፓናል ውይይት ተሳታፊዎች ለዚህም የአንድ ሃገር የነጻነት መገለጫ ለሆነው ለብሔራዊ ባንድራ ተገቢ ክብር መሰጠት ያስፈልጋል ያሉት።

በበሉ ላይ የሀላባ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የዞኑ ግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ ሀጂ ኑሪዬ፣ የሀላባ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ መሀመድአሚን ሀ/መሀዲ፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት፣ የማ/ኢ/ክ/የፍትህ አካላት ማሠልጠኛና የሕግ ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሽተባ አባድር፣ የክላስተሩ አመራሮችና ሰራተኞች፣ የዞንና የዌራ ወረዳ አመራሮችና ሰራተኞች እና የሀገር መከለያ አባላት፣ የፀጥታ አካላት ተገኝተዋል።

ምንጭ:- የሀላባ ዞን መንግስት ኮምኒኬሽን መምሪያ ።

← Back to News