follow_us:
📞 +251 911 898 192

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ የ"ሴራ" በዓልን ምክንያት ያደረገ የጎዳና ላይ ሩጫ በድምቀት ተካሄደ ። ጥር 1/2018 (ሀላባ ቁሊቶ)

📅 January 9, 2026 | 🖊️ Admin

News Image
 
የሀላባ ብሔር ማንነት እና ባህል መገለጫ የሆነውን የ"ሴራ" በዓል ምክንያት በማድረግ በዛሬው ዕለት በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ደመቅ ያለ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ።
​በውድድሩ ላይ በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ወጣቶች እና ስፖርተኞች የተሳተፉ ሲሆን፣ በከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ላይ በነበረው ሩጫ ከፍተኛ የሆነ የስፖርታዊ ጨዋነት እና የደስታ ስሜት ተስተውሏል።
ውድድሩ በበዓሉ ላይ የሚታየውን አንድነት እና ወንድማማችነት ይበልጥ እንዲጎለብት ለማድረግ የታለመ መሆኑ ተገልጿል።
​ከጅማሬ እስከ ፍጻሜው ከፍተኛ ፉክክር በታየበት በዚህ ውድድር ላቅ ያለ ብቃት ያሳዩ አትሌቶች የአሸናፊነት ክብርን ተቀዳጅተዋል።
በውድድሩ ማጠቃለያ ላይም ​ለአሸናፊዎች የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
​የዘንድሮው የሴራ በዓል በስፖርታዊ ውድድሮች ታጅቦ መከበሩ ለከተማዋ ልዩ ድምቀት የሰጠ ሲሆን፣ ተሳታፊዎችም በውድድሩ በመሳተፋቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
← Back to News