follow_us:
📞 +251 911 898 192

የቤት አስተዳደር ዘርፍን ዲጂታላይዝ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ምክክር ተካሂዷል።

📅 May 26, 2025 | 🖊️ Admin

News Image

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ጋር የቤት አስተዳደሩን ዘርፍ የአሰራር ስርዓት በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማዘመን ያለመ ነው።

ምክክሩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን ዓለማየሁ እና የሚኒቴሩ አመራሮች በፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በመገኘት የተካሄደ ሲሆን ተቋሙን ዲጂታላይዝ ለማድረግ የተሰሩ ስራዎችንም ጎብኝተዋል።

በተካሄደው ምክክር ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን ዓለማየሁ ኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ለማሳካት ሁሉም ተቋማት ከዘመኑ ጋር የሚሄድ፣ የተገልጋዮችን እርካታ የሚያረጋግጥ በሆነ መልኩ አገልግሎታቸውን በ ዲጂታል ስርዓት መስጠት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

አሰራሮችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ማዘመን የውዴታ ግዴታ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ተቋማት ሁለንተናዊ ስራዎቻቸውን ለማዘመን የሚያደርጉትን ጥረት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በቅርበት ሆኖ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የቤቶችና ይዞታዎች ማስከበርና ማከራየት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌቱ ዘውዴ የተቋሙ ስራዎችን ዲጂታላይዝ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሰራታቸውን አብራርተዋል።

አክለውም የቤት አስተዳደር ዘርፉን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማዘመንና የተሳለጠ የአሰራር ስራዓቱ ለመዘርጋት ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በትብብር ለመስራትና ድጋፍ እንዲደረግላቸው እንደሚፈልጉ ገልፀዋል።

news source Ministry of innovation and Technology (MinT)  #halaba_zone  #halaba

የዲጂታል አሰራሮች አቢዎት Video 

 

← Back to News