follow_us:
📞 +251 911 898 192

የዘመነ ዲጂታል ኢኮኖሚ የዕድገታችን መሰረት ነው'' በሚል መሪ ቃል የሀላባ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ከዞኑ ት/ት መምሪያ ጋር በመሆን የተዘጋጀ የፈጠራ ስራዎች ውድድር፣ ባዛር ፣ የፈጠራ ስራዎች ኤግዚቢሽን እና ፓናል ውይይት መድረክ ተካሄደዋል።

📅 May 23, 2025 | 🖊️ Admin

News Image
በጅምር ላይ ያሉ የፈጠራ ስራዎችን በመደገፍ ሙያዊ እገዛም በማድረግ ለተሻለ ውጤት ማብቃት ከሁሉም ይጠበቃል - አቶ አበበ አልዬ
 
ግንቦት 1/2017 "
የውይይት መድረኩን የመሩት የሀላባ ዞን ዋና አስተዳደር ማሀበራዊ ዘርፍ አማካሪ አቶ አበበ አልዬ እንደገለጹት ዓለም ዛሬ በቴክኖሎጂ ብዙ ርቀት የተጓዘ በመሆኑ እንደሀገር የፈጠራ ስራ ላይ ልዩ ትኩረት ማድረግ እንዳለብን ወቅቱ በራሱ ያስገድደናል ብለዋል።
በጅምር ላይ ያሉ የፈጠራ ስራዎችን በመደገፍ ሙያዊ እገዛም በማድረግ ለተሻለ ውጤት ማብቃት ከሁሉም እንደሚጠበቅ አቶ አበበ አልዬ ገልጸዋል።
በየትምህርት ቤቶችና በግል ደረጃ እየሞከሩ ያሉ የፈጠራ ውጤቶችን ህዝቡ እንዲያውቅ በማድረግ የፈጠራ ባለቤቶችን መደገፍ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
ትውልዱ በፈጠራ ስራዎቹ የማህበረሰቡን ኑሮ የሚያቀሉ ግኝቶችን እንዲያበረክት ለማድረግ ዘርፉን መደገፍና ማገዝ ጨምሮ ባለተስጥኦ ወጣቶችን መፍራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
የፈጠራ ተግባራትን ለመደገፍ ረገድ የባለድርሻ አካላት ርብርብ ወሳኝ በመሆኑ በማመላከት የዞኑ አስተዳደርም የሚጠበቅበትን ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንም አቶ ከድር አረጋግጠዋል።
አዳዲስ የፈጠራ ስራ የሚሰሩ ወጣቶች ፈጠራቸውን ትርጉም ባለው መልኩ የማህበረሰብ ችግር መፍቻ ለማድረግ በመምሪያው በኩል የጀመሩ ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።
የሀላባ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ሀላፊ አቶ መሀመድ ሀሰን በበኩላቸው መምሪያው ፈጠራ ሐሳብ ያላቸው ወጣቶች በስፋት አውጥተው እንዲያስተዋውቁ ከፈጠራ ባለቤቶቹ ጋር በቅንጅት እየተሠራ እንዳለ አስረድተዋል።
መምሪያው ለእነዚህ አካላት ከሀሳብ ጀምሮ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ መቆየቱን ሀላፊዋ ተናግረው ይህንን ይበልጥ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
በየዓመቱ በተማሪዎችና በግለሰቦች የተሰሩ የፈጠራ ውጤትች በኤግዚቢሽን መልክ ለህዝብ ክፍት ሆኖ እንዲተዋወቅ እየሠራ እንዳለም ገልጸዋል።
የፈጠራ ውጤቶችን ይዘው የቀረቡ ወጣቶችና ተማሪዎች ከወዳደቁ ቁሳቁስ የተለያዩ ችግር ፈቺ የፈጠራ ውጤቶችን ማፍለቅ ነው ብለዋል።
የሚመለከታቸው አካላት ያልተቆራረጠ ድጋፍ የሚደረግላቸው ከሆነ በዘርፉ የተሻለ ቴክኖሎጂ ማፍለቅ እንደሚችሉ አቶ መሀመድ አስገንዝበዋል።
በዕለቱ የፈጠራ ስራዎችን ለኢግዚቢትነት ላቀረቡ ተማሪዎች እና በዕለቱ ለተወዳዳሪ አሸናፊ ተማሪዎችም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በመድረኩ ላይ የሀላባ ዞን ትምርህርት መምሪያ ሀላፊ ዶክተር ኤፍሬም ዘለቀ፣ የዞን ማህበራዊ ዘርፍ አመራሮች፣ የአራቱም መዋቅር የሳኢቴ እና የትምህርት አመራሮች፣ የፈጠራ ባለቤቶች እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
በሹኩር ሀ/ሀሰን https://halabasit.gov.et/
← Back to News