follow_us:
📞 +251 911 898 192

የ2017 በጀት አመት የሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት 1ኛ ደረጃ

📅 August 28, 2025 | 🖊️ Admin

News Image

የ2017 በጀት አመት የሀላባ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አፈጻጸም እና ሽልማት

ነሀሴ 21/2017 የሀላባ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ የ2017 በጀት አመት ማጠቃለያ ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2018 ዕቅድ ላይ ውይይት መድረክ አካሄደዋል።

በዚህ የዞኑ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ በ2017 በጀት አመት ዕቅድ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ለታችኛ መዋቅሮች እውቅና ሽልማት ሰጥተዋል።

ሽልማት የተሰጠው በመዋቅሮች

  • የዌራ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት – 1ኛ ደረጃ
  • የዌራ ዲጆ ወረዳ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት – 2ኛ ደረጃ
  • የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት – 3ኛ ደረጃ
  • የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት – 4ኛ ደረጃ

በተጨማሪም ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ የወጡ የመምሪያ ማኔጅመንት አባላት እና ባለሙያዎች የእውቅና ሰርተፍኬት ተሰጥተዋል።

ታላቅ ኃላፊነት እና ምርጥ ስራ

ተመዘገቡ መዋቅሮች ከዞኑ አስተዳዳሪ ማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ከአቶ ሁሴን ሮባ፣ ከዞኑ ምክር ቤት ማህበራዊ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ከአቶ ሪባቶ ቤያጎ እና ከዞኑ ሳይንስና ቴክኖሎጂ መምሪያ ሀላፊ ከአቶ መሀመድ ሀሰን እጃቸው የተዘጋጀ የእውቅና ሽልማት ተቀብለዋል።

እውቅና ሽልማት ለተመዘገቡ ስኬቶች ብቻ ሳይሆን በቀጣይ ለሚሰሩ ተግባራትም ትልቅ ሀላፊነት እንዲሰጥ ይኖርበታል።

2018 ዓመት ዕቅድ እና ግብ ስምምነት

የዞኑ ሳይንስና ቴክኖሎጂ መምሪያ 2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ተግባራትን በጋራ ለመፈፀም ከመዋቅሮች ጋር የግብ ስምምነት ተፈራርመዋል።

በሹኩር ሀ/ሀሰን

← Back to News