follow_us:
📞 +251 911 898 192

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባለፉት በዘጠኝ ወራት ከ36,936 በላይ ዜጎች በኢትዮ ኮደርስ ስልጠና መውሰድ መቻላቸውን ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፈቃዱ ገለጹ

📅 May 23, 2025 | 🖊️ Admin

News Image
 
ሆሳዕና፣ግንቦት 14/2017
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ እንደገለጹት ባለፉት በዘጠኝ ወራት ከ36,936ሺ ዜጎች በኢትዮ ኮደርስ ስልጠና መውሰድ ችለዋል።
እንደ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፈቃዱ ገለጻ በበጀት ዓመቱ ለ49ሺ 549 ዜጎች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ለመስጠት ታቅዷል።
ስልጠናው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አሕመድ (ዶ/ር ) ሀሳብ አመንጪነት መገኘቱን የገለጹት አቶ አንተነህ በዚህ መልካም አጋጣሚ ዜጎች ተሳትፎ ማድረግ እንዳለባቸው ጥሪ አቅርበዋል።
ስልጠናው ዲጂታል ማህበረሰብ ለመፍጠር ለሚደረገው ጥረት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በብቃት ላጠናቀቁ ዜጎች የሚሰጠው ሰርተፍኬት አለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ከማሳደግ ባለፈ ለተጨማሪ የስራ እድሎች ምቹ መደላድል እንደሚፈጥርም ኃላፊው አብራርተዋል።
በክቡር ጠ/ሚኒስትር ጥረት የተገኘው የስልጠና ዕድል በግለሰብ ደረጃ ለመሳተፍ የሚጠይቀው በጀት ከፍተኛ ነው ያሉት ኃላፊው በነጻ የተገኘውን የትምህርት ዕድል በመጠቀም የቴክኖሎጂ ክህሎት ማሳደግ ተገቢ ስለመሆኑም ኃላፊው ጠቁመዋል።
በክልሉ የስልጠናውን ተደራሽነት ለማሳደግ ልዩ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር መገባቱን አቶ አንተነህ አመላክተዋል።
ስልጠናው የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ካለው የላቀ ጠቀሜታ አንጻር በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸውም አቶ አንተነህ አሳስበዋል።
credit toClick to Register Ethio coders Central Ethiopia Regional Government Communication Affairs bureau #halabanew #halabasit #ethiocoders
← Back to News