Halaba SIT
Halaba Kulito, Central Ethiopia +251 911 898 192
ያከታተሉን:
የሀላባ ዞን ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ መምሪያ በዌራ ወረዳ ጽ/ቤት የሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ላይ ትኩረት ያደረገ ድጋፍና ክትትል አካሄደ

የሀላባ ዞን ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ መምሪያ በዌራ ወረዳ ጽ/ቤት የሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ላይ ትኩረት ያደረገ ድጋፍና ክትትል አካሄደ

October 29, 2026 Admin 24 ቀን በፊት 27 ዕይታዎች
የስራ አፈጻጸም እና ክትትል
📅 ጥቅምት 18/2019 ዓ.ም | 📍 ዌራ

(ዌራ) — የሀላባ ዞን ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ መምሪያ የተመደቡ የማኔጅመንት አካላት የዌራ ወረዳ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤትን የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም በቦታው በመገኘት በቼክ ሊስት በመደገፍ ሰፊ የድጋፍና ክትትል ሥራ አከናውነዋል።

የመድረኩ ዋና ዓላማ

ይህ የድጋፍና ክትትል መድረክ በወረዳ ደረጃ የተከናወኑ ዋና ዋና የልማትና የቴክኖሎጂ ሥራዎችን አፈጻጸም ለመገምገም፣ በሂደቱ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ለመረዳት እንዲሁም በቀጣይ መሻሻል በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ የጋራ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በግምገማው የተዳሰሱ ዋና ዋና ጉዳዮች

በዕለቱ በተካሄደው ውይይት የጽ/ቤቱን የማኔጅመንት አባላት በመገኘት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ውስጥ የተከናወኑ አበይት ተግባራት በዝርዝር ተመልክተዋል። ከነዚህም መካከል፡-

  • የኢትዮ ኮደርስ (Ethio Coders) መርሃ ግብር፡ በዲጂታል ክህሎት ግንባታና በኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራትና የተመዘገቡ ውጤቶች።
  • የአይሲቲ (ICT) መሣሪያዎች ጥገና፡ ተቋማዊ አቅምን ለማጠናከርና አገልግሎትን ለማቀላጠፍ የተደረጉ የጥገናና የይዞታ አስተዳደር ሥራዎች።
  • ሳይንስና ፈጠራ (Innovation)፡ አዳዲስ አሰራሮችንና ፈጠራዎችን በማበረታታት በኩል የተሰሩ ስራዎች።
  • ሪፎርም እና መልካም አስተዳደር፡ የተቋሙን አሰራር ቀልጣፋ ለማድረግ የተነደፉ የሪፎርም ዕቅዶች አፈጻጸም።
  • የ100 ቀናት የስራ አፈጻጸም፡ በመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት ውስጥ ለማከናወን የታቀዱ እና የተፈጸሙ ዋና ዋና ስራዎች ግምገማ።

የተሰጡ አቅጣጫዎችና መደምደሚያ

የግምገማ መድረኩ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተከናወኑ ጠንካራ ጎኖች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ መድረክ የፈጠረ ነበር። በሌላ በኩል በሥራ አፈጻጸም ሂደት ውስጥ የታዩ ክፍተቶችና ተግዳሮቶች በግልጽ ተለይተው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን፤ በቀጣይ ጊዜያት ክፍተቶቹን በማረም የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገብ እንዲቻል ገንቢ ሐሳቦች፣ አስተያየቶችና ጠንካራ አቅጣጫዎች በመሰጠታቸው የድጋፍና ክትትል መርሃ ግብሩ በስኬት ተጠናቋል።


27 ዕይታዎች
1 ሼሮች