የሀላባ ከነማ መልእክት ማጠቃለያ
በተከታታይ 3 ጨዋታ ጠንካራ ክለቦችን አስተናግደን ጅማሬያችንን በሊጉ ልምድ ካላቸው ክለቦች በተሻለ አሳምረናል፡፡
ባለፉት 3 የቤታችን ጨዋታዎች በርበሬዎቹ ማራኪውን የኳስ ፍሰት ይዘው ለሊጉ ክስተት ሆነው መቅረባቸውን በተግባር ማስመስከርም ጀምረዋል፡፡
እስካሁን ባደረግናቸው ጨዋታዎች በሊጉ ከከረሙ ክለቦች በተሻለ መልኩ ያሳየነው ድንቅ ብቃት እጅግ የሚያስደስት ጠንካራ የቡድን ቁመና እንዳለን አመላካች ነው፡፡ ሆኖም ይህ አኩርቶ የሚያስቆመን ሳይሆን የበለጠ የሚያጠናክረን ነው፡፡
በሌላ በኩል በሀገሪቱ የእግር ኳስ ውድድሮች ደረጃ የተቀዛቀዘውን የደጋፊዎች ድባብ በመመለስ ለመላው የኢትዮጵያ ስፖርት አፍቃሪያን መነቃቃትን መፍጠር መቻላችን በራሱ ተጨማሪ ድል ነውና መላው የክለባችን ደጋፊዎች በሀላባ ከነማ ስም ዛሬም ከልብ እናመሰግናለን!!
እንግዲህ በዚህ ሳናበቃም በቀጣይ ጨዋታዎች እንደ ክለብ የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ እንዲሁም እንደ ደጋፊ የበለጠ ድባብ በመፍጠር የፕርሚየር ሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪነታችንን አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል!! ደግሞ እናሳካዋለን!!